በጤና - BE`TENA

Health and Wellbeing Platform

በጤና

በሃገራችን የመጀመሪያው ብቁና የነቃ ትውልድን ለመፍጠር የተዘጋጀ የናንተው የጤና አማካሪ!

ውበት አጠባበቅ

ቤተሰብ ይሁኑ!

ጤናማ አመጋገብ

ቤተሰብ ይሁኑ!

የውይይት መድረክ

ቤተሰብ ይሁኑ!

የሚያሸልሙ ጥያቄዎች | የልምድ ልውውጥ | ውበት አጠባበቅ ጤናማ አመጋገብ | የምክክር መድረክ እና . . . ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች


ደም ማነስ
(anemia)

ደም ማነስ: ምንነት

  • ደም ማነስ ማለት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ቀይ የደም ሴል(Red blood cell) መጠን መቀነስ ማለት ነው።
  • ቀይ የደም ሴል ዋና ተልዕኮው ኦክስጅንን ከሳንባ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዲሁም ካርቦንዳይኦክሳይድን(Co2) ከሰውነታችን ወደ ሳንባ ማመላለስ ነው። ስለዚህ ደም ማነስ ሲኖር ይህ ስርአት ስለሚዛባ ሰውነታችን በቂ ኦክስጅን አያገኝም
  • ደም ማነስ የሌላ በሽታ ምልክት እንጅ በራሱ በሽታ አይደለም

አጋላጭ ነገሮች

  • ብዙ ደም መፍሰስ
  • የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ
  • ከላይ የተጠቀሱና ሌሎች የተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ መሆን
  • ለተለያዩ ኬሚካሎች(arsenic, benzene,chemotherapy…)ና ጨረር ተጋላጭ መሆን
  • በቤተሰብ ደም ማነስ ያለበት ካለ

ሳል

  • ብዙ ጊዜ አጣደፊ የሆነ የአጭር ጊዜ (ከሶስት ሳምንት ያነሰ) ወይም የረጅም ጊዜ (ከአራት ሳምንት) የዘለለ ሊሆን ይችላል።
    የሳል ምክናየቶች
    • ጉንፋን, ኢንፊሎወንዛ, አለርጅ, የብናኝና ኬሚካል መግባት, የሳንባ ምች, ትክትክ በሽታ, ቲቢ, አስም, የብሮንከስ ኢንፌክሽን, የጉሮሮ በሽታ, የሳይነስ ኢንፌክሽን, የፈሳሽና አየር ሳንባ ውስጥ መጠራቀም, ሌሎችም

ሳል ማስታገሻ መንገዶች

  1. የማር ሻይ
  2. በቂ ፈሳሽ መውሰድ
  3. ስቲም ወይም እንፋሎት መጠቀም
  4. ጨው ባለው ውሀ ጉሮሮን መጉመጥመጥ ወይም ማኩረፍረፍ
  5. ፍራፍሬ እንደ ብርቱካን አይነት መጠቀም
  6. የአናናስ ጁስ መጠጣት እና ሌሎችም

ቁርጥማት (አርተራይተስ)

  • የአለም አቀፍ የአርተራይተስ (የቁርጥማት) ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለሽታው ግንዛቤ ለማስጨበጥ በጥቅምት 02 ይከበራል፡፡ ይኸ ቀን በአለም ደረጃ ከ 1966 ጀምሮ እየታሰበ ይገኛል፡፡ በዚህም አመት ለ26 ጊዜ ይከበራል፡፡

  • በአርተራይተስ ቀን ግንዛቤ የማስጨበጥ ትኩረቱ በአጠቃላይ የስነ- ቁርጥማት ፤ጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት (Rheumatic and Musculoskeletal Disorders) ህመሞችን ያጠቃለለ ነው፡፡

ምልክቶቹ

  • የመገጣጠሚያ ህመም ፤ እብጠት እና ተፈጥሮአዊ ቅርፅ መዛባት፡፡ 

  • ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ መላ ሰውነት መተሳስር፤ ልብስ ለመልበስ እና የግል ንፅህናን ለመጠበቅ መቸገር፤ ቀኑ ረፈድ እያለ ሲሄድ ሰውነትን ለቀቅ ማደረግ፡፡ 

  • ይኸ በዋናነት በእጅ እና እግር ጣቶች ላይ በርትቶ ቢስተዋልም ሁሉንም መገጣጠሚያዎች ያጠቃል፡፡

ጤናችን ትልቁ ሃብታችን ነው!

በጤና

አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ . . .

ሃሳብ አስተያየትዎን ያጋሩን

Scroll to Top